top of page

እንኳን ደህና መጣህ

ውድ የSouth Shore ኮምዩኒቲ

የSouth Shore የወላጆች፡ መምህራንና ተማሪዎች ማህበርን በመወከል ወደ ትምህርት ቤት ለሚመለሱት ቤተሰቦች፡ መምህራንና ሰራተኞች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ለትምህርት ቤቱ ኣዲስ ለሆኑት ደግሞ ሰለምታቻንን እናቀርባለ።

የእናንተንና የቤተሰቦቻችሁ ጤና የተጠበቀ ኣንደሆነ እየተመኘን ይህንን ቆንጆ ክረመት እየተደሰታችሁበት ለመሆናችሁ ተስፋ እናደርጋለን። የምህርት ዓመቱ ምንም ይኑሮው ምን፡ ለማይበግረው የምሁራንና ታታሪው የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች ኮምዩኒቲ በማመስገን እያንዳንዱን ተማሪ በትምህቱንና በእድገቱ ሂደት ውስጥ ለመርዳት ከልብ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን።

የSouth Shore የወላጆች፡ መምህራንና ተማሪዎች ማህበር የተመሰረተው ለየትምህርት ቤቱ ኮምዩኒቲ ፍላጎቶችን ከፍ ኣድርጎ ጥብቅና በመቆም፡ ተማሪዎችን በክፍል ውስጥም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጭ መርዳትና የኮምዩኒቲ ተሳትፎና ግንኙነት ማጠናከር ነው።

ይህንንም ስራ እውን እየሆነ ያለው ደግሞ በእርስዎ ምክንያት ብቻ ነው። እንደ ኣባላት በነጻ የማገልገል ወይንም እርዳታ የማበርከት ግዴታ ባይኖርባችሁም እንደ ወላጅ፡ መምህር፡ ተንከባካቢና የኮምዩኒቲ ኣባላት መጠን የወላጆች፡ መምህራንና ተማሪዎች ማህበር ስራዎች ከቅድሚያዎቻችሁ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የናንተ ድምጽ ኣስፈልገናል።

የ2021-22 የባልነት ቅጻችን በማያያዝ እያንዳንዱ ኣዋቂና (ጎማሳ) በቤተሰባችሁ የሚገኝ የመለስተኛ 2ኛ ደረጃ ተማሪ ቀጥለው በተዘረዘሩት 4 የኣባላት ስብሰባዎች መምረጥ ኣንድትችሉ፡ ተለእኮኣችንና ራኢያችን ለማሻሻል እንድትረዱን፡ ተማሪዎቻችን ለመርዳትና ከኣመቺ ዕድሎች ጋር ለማገናኘት እንድንችል የዚህ ዓመት ኣባልነታችሁ እንድታሳድሱ ወይንም እንደ ኣዲስ እንድትጀምሩ እናሳስባለን።

በእንድነት የእያንዳኑን ተማሪ እድገት ማረጋገጥ እንችላለን!

እባክዎትን፡ በዚህ ጉዞ ይቀላቀሉን


በኣክብሮት

ሆዳን መሓመድና መጋን ስፕርጅዮን

የSouth Shore የወላጆች፡ መምህራንና ተማሪዎች ማህበር ተባባሪ ሊቀመናብርት




2021-22 Member Meetings

October 20, 2021 | 6:00pm

January 19, 2022 | 6:00pm

April 20, 2022 | 6:00pm

May 18, 2022 | 6:00pm




4 views0 comments

Comments


bottom of page